Ethiopian Review Readers Forum

Ethiopian Review Readers Forum
Start a New Topic 
Author
Comment
Woyane Sinking Sinking Sinking deeper

ሠራዊቱ ጥያቄ አነሳ
በሀገሪቱ የሰፈነውን ውጥረት ተከትሎ በጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ የተዘጋጀው ፅሁፍ በካድሬዎች አማካይነት በሰራዊቱ ውስጥ ውይይት እየተደረገበት ሲሆን፣ የአውሮፓ ህብረት መግለጫ ካወጣ በኋላ በየስብሰባው አዳራሽ በኢህአዴግ መንግሥት ላይ ጠንከር ያሉ ጥያቄዎች መነሳት ጀምረዋል። «እኛ የምንጠብቀው ህገ-መንግሥቱን ነው ወይንስ ኢህአዴግን?» የሚለው ጥያቄ በሰራዊቱ የውይይት መድረኮች በስፋት የተስተጋባ ሲሆን፣ ኢህአዴግ በምርጫው ከተሸነፈ ስልጣኑን የማይለቀው ለምንድን ነው? የሚሉ ጥያቄዎችም ተነስተዋል። በጠ/ሚ/ሩ የተዘጋጀውን መፅሐፍ ይዘው ውይይቱን የመሩት ካድሬዎች ያጋጠማቸውን ተቃውሞ መቋቋም እንዳቃታቸው፣ በሰራዊቱ በኩል ምርጫውን በተመለከተ የሚነሱ መከራከሪያዎችን ለማሸነፍ መቸገራቸውን የመጣው ዜና ያብራራል።

ይህ በየደረጃው ወደ ሰራዊቱ ይወርዳል በሚል የተጀመረው ውይይት በአሁኑ ወቅት ያተኮረው በሰራዊቱ ከፍተኛ አመራር ላይ ነው።

«ኢህአዴግ ዋሽቶናል፤ ምርጫ ቦርድም ገለልተኛ መሆኑ አጠራጥሮናል» የሚሉ የተቃውሞ ድምጾች በተሰሙበት የሰራዊቱ አመራሮች የውይይት መድረክ «እኛ ህገ-መንግሥቱን አስከባሪና ጠባቂ እንደመሆናችን ማንም ይሁን ማን ይህንን ህገ-መንግስት ሲጥስ እያየን ዝም አንልም» የሚል አስተያየትም ተሰንዝሯል። «እኛ የህገ-መንግስቱ እንጂ የኢህአዴግ ጠባቂዎች አይደለንም» የሚለው በየውይይቱ መድረክ ጐልቶ የወጣና በሰራዊቱ አመራር ዘንድም ድጋፍ ያገኘ አስተያየት መሆኑን መረዳት ተችሏል።በአዲስ አበባ፣ በደብረዘይት፣ በመቀሌ፣ በባህርዳርና በሌሎችም ስፍራዎች የተጀመረውን ይህንን ውይይት የሚመሩት ካድሬዎች በተለይ የአውሮፓ ህብረት ታዛቢ ቡድን የምርጫ ውጤት ከተገለጸ በኋላ ከሰራዊቱ መኮንኖች የሚሰነዘሩ አስተያየቶችንና የተቃውሞ ድምጾችን መቋቋም እንደተሳናቸው ተሰምቷል። በአንዳንድ መድረኮች አወያዮቹ የማይሆን ምላሽ ለመስጠት በመሞከር ውይይቱን ወደ ውጥረት የከተቱበት ሁኔታ ሲመዘገብ፣ በሌሎች መድረኮች ደግሞ አወያዮቹ ከበላይ አካል ማብራሪያ እንጠይቃለን የሚል ምላሽ በመስጠት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅሁፍ ላይ ሲወያዩ ቆይተዋል።

ከበላይ አካል በወረደ ትዕዛዝ ውይይቱ ለጊዜው ከተቋረጠ በኋላ አወያዮቹ በሙሉ ትናንት አዲስ አበባ ገብተዋል። ትናንት ምሽትም ስብሰባ ተጠርተዋል። ይህም ስብሰባ ከሰራዊቱ የተነሱትን ጥያቄዎች በተለይም የአውሮፓ ህብረትን መግለጫ ተከትሎ የተነሳውን ጠንካራ ትችት መመከት በሚያስችልበት ሁኔታ ላይ አወያዮቹን ለማዘጋጀት እንደሆነ የታመነበት ሲሆን፣ የውይይቱን ዝርዝር ግን ማግኘት አልተቻለም። ጠ/ሚ/ር መለስ ባለፈው ዕሁድ በእንግሊዝኛው የኢትዮጵያ ሄራልድ ጋዜጣ ላይ የአውሮፓ ህብረትን መግለጫ «ለእኔ በጣም አስደንጋጭ ነው» ሲሉ መጻፋቸው፣ «የህብረቱ መግለጫ ቁጣን ቀስቅሷል» ሲሉ ማከላቸው የህብረቱን መግለጫ ለመተቸት የፓርቲያቸውን ውሳኔ ሳይጠብቁ በግል፣ በፍጥነት ምላሽ መስጠታቸው ምናልባት ከሰራዊቱ ተቃውሞ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።

Re: Woyane Sinking Sinking Sinking deeper

In your Dream !!! EPRDF -is breathing and kicking !!! don`t forget stronger than Ever! !!

Re: Woyane Sinking Sinking Sinking deeper

Nice wish Lulit!

Re: Woyane Sinking Sinking Sinking deeper

sunk!!!!!

Email: messayewossen@yahoo.com

City: los angFORels

Re: Woyane Sinking Sinking Sinking deeper

You will see the inevitable soon