Ethiopian Review Readers Forum

Ethiopian Review Readers Forum
Start a New Topic 
Author
Comment
REPORTER- becoming more like IFTIN, its sibling

ጠ/ሚ/ር መለስ 1ሺህ 200 ኢትዮጵያውያን ሰልፍ ወጡባቸው
የኖርዌይ ማዳበሪያ አምራች እና አከፋፋይ የሆነው «ያራ» ባለፈው ቅዳሜ ለጠ/ሚ/ር መለስ ዘናዊ ሽልማት በሰጡበት ወቅት ጠ/ሚ/ር መለስ ከፍተና ተቃውሞ የገጠማቸው ሲሆን፣ በተቃውሞ ትዕይንቱ የተደናገጡት የያራ ኩቡአንያ ሃላፊዎች ጠ/ሚ/ሩን በጓሮ በር ለማስገባት ተገደዋል፤ ይህ በእንዲህ እንዳለም፣ በስካንዲኒቪያን ሐገሮች የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑ ግለሰብ በኖርዌይ በጠሩት ስብሰባ ላይ ለሰኔ አንድ ሰማዕታት የህሊና ፀሎት አላደርግም በማለታቸው በተፈጠረ ውዝግብ፣ ሰውየው የኖርዌይ ፖሊሶችን ጠርተው ኢትዮጵያውያንን ካሰከበቡ በኋላ፣ ስብሰባት ተቋርጧል።

በማዳበሪያ ንግድ የታወቀው የኖርዌይ ኩባንያ «ያራ» በ50 ዓመት ታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀውን ይህንን ሽልማት፣ ከራሱ 50ኛ ዓመት በዓል ጋር አብሮ ያስኬደው ሲሆን፣ የኖርዌይ ጠ/ሚ/ር ሚስተር ሼልማግነ ቡንዲቪክን ጨምሮ የኖርዌይ ባለሥልጣናት በትዕይንቱ ላይ እንደማይገኑ በገለፁት መሰረት በፕሮግራሙ ላይ አልታደሙም፤፡

በኖርዌይ ነዋሪ የሆኑ አንድ የሰልፉ ታዳሚ ስለዚህ ጉዳይ ለጀርመን ድምፅ ሲናገሩ፤- «የኖርዌይ ጠ/ሚ/ር እናሌሎች ባለሥልጣናት ከመነሻው አንገንም ማለታቸው መልዕክቱ «አንፈልግህም» ማለት በመሆኑ ሰውየው ሞራል ቢኖረው ኖሮ አይመጣም ነበር» ሲሉ ተደምጠዋል፣ ጠ/ሚ/ሩ ወደ ሽልማቱ ስፍራ ሲደርሱ በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ባሰሙት ተቃውሞ ሳቢያ ጠ/ሚ/ሩ ፊት ለፊት ሳይሆን፣ በጓሮ በር ለመግባት ተገደዋል፦ ስለዚህ ጉዳይ ሌላ የትዕይንቱ ታዳሚ ሲገልፁ፦ «በጓሮ በር፣ በትንሽ በር መግባታቸው ለርሳቸው ታላቅ ውርደት በመሆኑ፣ እኛ ኢትዮጵያውያን ታላቅ ደስታ ተሰምቶናል» ብለዋል።

የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት በኦስሎ ጐዳናዎች ያሳዩቱ ትዕይንንትና ወደ ሽልማቱ አዳራሽ ያደረጉት እንቅስቃሴ፣ ከጠ/ሚ/ሩ ሽልማት በላይ የጋዜጠኞችን ትኩረት የሳበ እንደነበር መረዳት ተችሏል፤ እስከዛሬ በኦስሎ ውስጥ ኢትዮጵያውያን በዚህ መጠን አደባባይ ወጥተው ተቃውሞ አድርገው አያውቁም። ለተቃውሞ አደባባይ የወጡት ሰልፈኞች የኖርዌይ ጋዜጠኞች ከ1 ሺህ 200 በላይ መሆናቸውን ሲገልፁ፣ በአዲስ አበባ የሚታተመው «ሪፖርተር» ጋዜጣ የሰልፈኞቹ ብዛት ከ50 እስከ 80 ነው ብሎ አስፍሯል፤ ከነዚህም ውስጥ 20 ያህሉ የሻዕቢያ ደጋፊ ኤርትራውያን ናቸው የሚል ዘገባ አቅርቧል፤ ለሻዕቢያ የሚቀርበው ማነው? የሚለውን ጥያቄ ብዙዎች ያነሱ ሲሆን፣ ከ1 ሺህ 200 በላይ ኢትዮጵያውያን የተገኙበትን ትዕይት ሪፖርተር 50 ሰው በሚል የተዛባ ዘገባ ማቅረብ የተፈለገበት ምክንያት በውል ባይታወቅም፣ ኢህአዴግ በውስጥም፣ በውጭም ተቃውሞ እየበረታበት መሆኑን እንዳይታወቅ የሚደረግ ሙከራ እንደሆነ በብዙዎች ዘንድ የሚታመንበት ሆኗል፤ ከትናንት በስቲያ ሰኞ ለንባብ የበቃው ኦፍተን ፖስተን የተባለው የኖርዌይ ጋዜጣ ባቀረበው ዘገባ፣ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡትን ኢትዮጵያውያን ብዛት ከአንድ ሺህ በላይ በሚል ያስፈረ ሲሆን፤ ከስብአዊ መብት ድርጅቶችና ከኢትዮጵያውያን ሽልማቱ ከፍተኛ ተቃውሞ የቀረበበት መሆኑንም አስፍሯል።

ከኢትኦጵ ጳጉሜን 2 ቀን 1997

Re: REPORTER- becoming more like IFTIN, its sibling

The brothers IFTIN. REPORTER, WALTA, are trying to turn back the hands of time!

Re: REPORTER- becoming more like IFTIN, its sibling

It is not cool to expect all news papers to write what we want to read. In my humble view Reporter is more crediable than the tabloid ethiohop

Email: haile#hotmaol.com

Re: REPORTER- becoming more like IFTIN, its sibling

Reporter is representing Woyane, masquarding as an independent newspaper.
Watch out how they contact foreign journalists

Re: REPORTER- becoming more like IFTIN, its sibling

The media should have presented the correct information. There were three groups at this hooligan walk.

1. The Mogadishu warlord supporters
2. Shaebia
3. CUD

Do you know what the percentages were?

Shabia has been preparing for this since the award was given, they were waiting for the date.