Ethiopian Review Readers Forum

Ethiopian Review Readers Forum
Start a New Topic 
Author
Comment
MAY GOD BLESS THE COURAGEOUS ETHIOPIAN PEOPLE!!!!!!!

SPECIAL MESSAGE TO THE GOVERNMENT OF ETHIOPIA::: NO ENOUGH POWER, TO SILENCE THE WILL AND THE VOICE OF THE PEOPLE!!!!!ETHIOPIANS ARE CAPABLE OF CALMLY AWAITING AN OUTCOME OF ANY RESULTS,,,BUT THAT DOESN'T MEAN THEY ARE POWERLESS!!!!! OH NO!!!

SPECIAL MESSAGE TO SHIEK AL AMOUDIN:: NO ENOUGH MONETARY GIFTS TO SILENCE THE WILL AND THE VOICE OF THE PEOPLE. ETHIOIAN PEOPLE ARE NO FOOL, THEY KNOW THEIR TRUE FRIENDS.


አዲስ አበባ ስታዲየም ትናንት በተደረገው የአትሌቶች አቀባበል በተቃውሞ ተናወጠ!
በ10ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከዓለም የሶስተኛነትን፣ ከአፍሪካ የመሪነቱን ስፍራ የጨበጠው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በአዲስ አበባ ስታዲየም የጀግና አቀባበል ሲደረግለት፣ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት ደግሞ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። ህዝቡ የሚናገሩትን ላለመስማት ስታዲየሙን በጩኸት ሲያናውጥ የዋለ ሲሆን፤ «ሌባ» የሚል ተቃውሞ አሰምቷል፣ የሼህ መሐመድ አልአሙዲን ስም ሲነሳ ቁጣውን በከፍተኛ ስሜት የገለፀው የስታዲየሙ ታዳሚ፣ በቅንነት አል አሙዲን ያደረጉትን አስተዋጽኦ ያመሰገነችው ጀግናዋ አትሌት መሰረት ደፋርም ከስታዲየሙ ስትወጣ መጠነኛ ተቃውሞ ገጥሟታል። የኢትዮጵያ አትሌቶች ያገኙትን ከፍተኛ አንፀባራቂ ድል በተመለከተ የህብረቱና የቅንጅቱ መሪዎች አድናቆትና ክብራቸውን ገልፀውላቸዋል፤ የኢትዮጵያ ጀግኖች እጅግ አኩሪ የሆነ ድል በመጨበጥና ተከታትለው በመግባት ዓለምን ያስደመሙበት ውጤት፣ በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ደስታን የፈጠረ ቢሆንም፣ በሐገሪቱ የሰፋ የፖለቲካ ውጥረትና ኢህአዴግ በጉልበት ለመቀጠል የሚያደርገው ዝግጅት በድሉ ላይ ጥላውን አጥልቷል።

ለወትሮው የነሃስ ሜዳሊያ ሲገኝ እንኳን በውድቅት ሌሊት ደስታውን ለመግለፅ አደባባይ ይወጣ የነበረው ህዝብ፣ ኢትዮጵያውያን ከአንድም ሁለት ከወርቅ እስከ ነሃስ ያለውን ጠራርገው ሲወስዱ፣ ትንሿ የኢትዮጵያ እንቁ ጥሩነሽ ዲባባ ታሪክ ስትሰራ በከተማው የመኪና ጥሩምባ ድምፅ እንኳን አልተሰማም፣ ሆኖም ህዝቡ አደባባይ ባይወጣም፣ ደስታውን በቤቱ መግለፁ ከቤቱም ውጭ ማውራቱ አልቀረም። ማንም በሚስማማበት ሁኔታ በሐገሪቱ የሰፈነው ውጥረት የድሉን ስሜት አደብዞታል።

አትሌቶቹ ከፊንላንድ መዲና ሄልሲንኪ ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉት በረራ በተለያዩ ሀገራት ከተሞች እያረፉ በመሆኑ፣ ቢሊየሩ መሐመድ አልአሙዲን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በግላቸው በመከራየት፣ አትሌቶቹ በቀጥታ በረራ አዲስ አበባ እንዲገቡ አድርገዋል፤ ሼህ መሀመድ አላሙዲን ከዚህ ቀደም ለአትሌቶቹ እንዲህ አያለ አስተዋፆኦ ወይንም ትብብር ሲያደርጉ ስላልታዩ፣ የአሁኑ ርምጃቸው፣ የንብ ካኒቴራ በመልበሳቸው የደረሰባቸውን ህዝባዊ ቁጣ ለማለዘብ እንደሆነ ታምኖበታል፤ ይህንን የሼህ መሐመድ አልአሙዲን ርምጃ «ላይቆጠርልሽ...» በማለት ከመነሻው ያጣጣሉት ጥቂቶች አልነበሩም፤ ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲየም ለአትሌቶች አውሮፕላን ተከራይተው ያቀረቡት ሼህ አልአሙዲን መሆናቸውን በመግለፅ የመድረክ መሪዎቹ ጭብጨባ ሲጠብቁ፣ የነበረው ምላሽ ግን ያልተቋረጡ የተቃውሞ ጩኸትና ማጉረምረም ነበር።

በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ስታዲየም አትሌቶቹን ለመቀበል የተገኘው ህዝብ አትሌቶቹ ከመድረሳቸው በፊት በሙዚቃ ባንድ የሚቀርቡ ሙዚቃዎችን እያሰማ ደስታውን ሲገልፅ ቆይቷል፤ አትሌቶቹ ስታዲየም ሲገቡም ከዳር እስከ ዳር ከመቀመጫው በመነሳት በከፍተኛ ጭብጨባ፣ ተቀብሏቸዋል፤ በዚህ በደስታ ስሜት እየጨፈረ፣ ኢትዮጵያ እያለ እየዘመረ የቆየው ህዝብ፣ ስሜቱ የተለወጠውና ወደ ተቃውሞ የተሸጋገረው የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባለሥልጣናት የኢህአዴግ ተጠሪዎች ንግግር እንዲያደርጉ በተጋበዙበት ወቅት ነው።፡ህዝቡ የነርሱን ንግግር ላለመስማት ባልተቋረጠ ጩኸት ስታዲየሙን አናውጧል፤ አቶ ተሾመ ቶጋ በከፍተኛ ተቃውሞ መሃል አድማጭ በሌለበት ሁኔታ ንግግራቸውን ሲጨርሱ፣ ጊፍቲ አባሲያ ተራቸውን እንዲናገሩ ሲጋበዙ፣ ላለመናገር ካንገራገሩ በኋላ፣ ርሳቸውም በጩኸት መሃል ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

የአቶ አርከበ ተወካይም ጩኸት ሳይለያቸው አጭር ንግግር አሰምተዋል። ሁኔታው በአንዳንድ አትሌቶች ላይ መገረምን፣ በአንዳንዶቹ ላይ ደግሞ ድንጋጤን ማስከተሉን ከገፅታቸውም ለመረዳት ተችሏል፤ በዚያ ሁሉ ተቃውሞ መሃል ድንገት የአትሌቶቹ ድምፅ ሲጠራ፣ የድጋፍ ጭብጨባና ጩኸት ተቃውሞ ይተካዋል፤ በዚህም የተነሳ ባለሥልጣናቱና ሌሎች የአበባ ጉንጉን ያደረጉት በፍፁም ጥድፊያ ሲሆን፤ ፕሮግራሙም የተጠናቀቀው በጥድፊያ ነበር፤ የኢህአዴግ ተወካዮች ህዝቡ እንደማይሰማቸው ከተገነዘቡ በኋላ ንግግራቸንው ትተው አትሌቶቹ ከህዝብ ጋር ሰላምታ የሚለዋወጡበትን፣ ምስጋና የሚያቀርቡበትን መድረክ ለማመቻቸት ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ፕሮግራሙ በግርግር ለመፈፀሙ ምክንያት እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ያስረዳሉ፤ በአዲስ አበባ ስታዲየም ትናንት በኢህአዴግ ባለሥልጣናት ላይ ህዝቡ ያሳየው ተቃውሞ፣ የህዝቡ ስሜትና አንድነት ተጠብቆ የቀጠለ መሆኑን ያረጋግጣል የሚሉት ታዛቢዎች፣ በስታዲየሙ ላልተገኘው ከአዲስ አበባ ውጭ ላለው ህዝብ ጭምር ከፍተኛ መነቃቃትን የፈጠረ ነው ሲሉም ይገልፃሉ፣ ሁኔታው ለኢህአዴግም ተጨማሪ የማስጠንቀቂያ ደወል እንደሆነም ተሰምሮበታል።

ከኢትኦጵ ነሐሴ 11 ቀን 1997

ሰለ እዚህ ዜና ዋርካ ስር በአማርኛ ይወያዩ !