Ethiopian Review Readers Forum

Ethiopian Review Readers Forum
Start a New Topic 
Author
Comment
ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ካለፈቃዳቸው ሀገር ቤት ሊመለሱ ነው

ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ካለፈቃዳቸው ሀገር ቤት ሊመለሱ ነው
የኢህአዴግ መንግሥት በስዊዘርላንድ ካለቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ የሚኖሩ 1400 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከአገር የመመለሱ ሥራ መጀመሩን በስዊዘርላንድ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ተወካይ አቶ ምስጢረ ኃይለ ሥላሴ አስታወቁ።

ተወካዩ ሰሞኑን አሜሪካ ለሚገኘው ለአዲስ ድምፅና ስዊድን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ድምፅ ራዲዮ እንደገለጡት የአቶ መለስ መንግሥት ላለፉት 14 ዓመታት የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አስመልክቶ ይከተል የነበረውን ፖሊሲ ቀይሮ ስደተኞቹ እጅ ሲሰጡ ሊሲ ፓሴ በመስጠት ወደ ሀገር እንዲመለሱ ማድረግ ጀምሯል።

ይኸው ርምጃ በዚሁ ከቀጠለ በአራቱ ስካንዲቪያን አገሮች ማለት በዴንማርክ፣ በስዊድን፣ በኖርዌይና በፊንላንድ የሚኖሩ 6000 ያህል ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን ስደተኞችም ተመሳሳይ እጣ ይገጥማቸዋል ተብሎ ተሰግቷል።